ለዚህ ጽሁፍም የተለያየ መጠን ያላቸውን ቱቦዎች የሚያመርት የህንዱን አምራች ኩባንያ ዊልስፑን ኮርፖሬት ሊሚትድን ምስክርነት ስንመለከት የምርቱን ጥራት ለማረጋገጥ እና ቀጣይነት ያለው ለውጥና መሻሻልን ለማምጣት የጥራት ሥራ አመራሩን (ISO 9001:2015 quality management system) በመተግበሩ አንኳር ለውጦችን ሊያይ እንዳስቻለውና በዓለም አቀፉ የንግድ መድረክም ተወዳድሮ እንዲያሸንፍ እንደ አንድ መሳርያ እንዳገለገለው የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ይገልጻሉ። አያይዘውም ስርዓቱ በሁሉም ስራ ቀዳሚው ጥራት መሆኑን እንዳስገነዘባቸውና አገልግሎቶቻቸው በሳይንሳዊ መንገድ ከወቅቱ ፍላጎት ጋር እንዲያራምዱ እገዛ እንዳደረገላቸው ገልጸዋል። ስለሆነም ይህ የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፤

መልካም አሰራርን ማስቀጠል መቻሉ

እንደ ድርጅቱ የጥራት ተቆጣጣሪ ገለጻ የአሰራር ስርዓቱን በመትከል በሚገኘው ሰርቲፊኬት ላይ ማተኮር ብቻ ሣይሆን በእያንዳንዱ የምርት ሂደት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ቀጣይነት ያለው የለውጥና የምርት ማሻሻያ ሥርዓት እንዲኖር በመሥራታችን ጥራት ያለው ምርት እንድናመርት አስችሎናል። ቀጣይነት ያለው የለውጥ ማሻሻያ ማለት ደግሞ የስራዎቻችን ትክክለኛነት የመመዘንና የማረጋገጥ (calliberation and validation) ተግባራትንም ይጨምራል።

ግልጽ የአሰራር ስርዓት መትከል ማስቻሉ

የአሰራር ስርዓቱ ስራዎች በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች እንዲከወኑ ስለሚፈቅድ ግልጽና ጥራት ያለው፤ ሁሉም የሚተማመንበትን ስርዓት እንዲዘረጉ ጠቅሟቸዋል። ደንበኞቻቸውም በየዕለቱ ስለሚቆጣጠሯቸው አሠራራቸውን በየወቅቱ እንዲፈትሹ ረድቷቸዋል።

ሥራን በውዴታና በተነሳሽነት እንዲተገበር ማድረጉ

አዲሱ ደረጃ በጥሬ እቃ ግዢና አቅርቦት እንዲሁም በማምረት ሂደት የሚኖርን ሥጋት በሥርዓት ለመፍታት ከማገዙም ባሻገር በምርቶች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የውስጥና የውጭ ተግዳሮቶችን በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት አስችሏል።

(ምንጭ: Nov-Dec 2015 ISO focus page 6-14)