በሰርቲፊኬሽን፡ በምርት ስርቲፊኬሽን ለ78 አዲስ ድርጅቶች የጥራት መስፈርትን በሟሟላታቸው የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል። ለ723 በምርት ሰርቲፊኬሽን ነባር ድርጅቶች ላይ ክትትል በማድረግ የፈቃድ እድሳት አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለ36 የማበጠሪያ ቤት ድርጅቶች አዲስ የማበጠር ፈቃድ ፣ለ169 ነባር የማበጠሪያ ቤት ድርጅቶች የማበጠር ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለ2 አዲስ ድርጅቶች የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ሰርቲፊኬት ተሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ በሰርቲፊኬሽን 1‚026 የአገልግሎት ጥያቄዎች ተስተናግደዋል፡፡

አሁን አገራችን ከደረሰችበት የኢኮኖሚ እድገት እና ኢኮኖሚው ከሚፈልገው ደረጃውን የጠበቀ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎትን በብቃት ለተጠቃሚዎቹ ከመስጠት አንፃር ገና በርካታ ክፍተቶች ያሉበት ሲሆን አመራሩና አጠቃላይ የተቋሙ ማህበረሰብ ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለጋራ ዓላማ መስራት ይጠበቃል፡፡ ለዚህም አሁን የተጀመረውን ተቋሙን በከፍተኛ ደረጃ የማስፋፋት እና የማዘመን ስራዎች በጋራ ሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ እራሱን በሁሉም መልኩ ማዘጋጀት የሚጠበቅበት ሲሆን  በቀጣይም በጀት ዓመት በዚህ ረገድ ዘርፈ ብዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች ይሰራሉ፡፡

በ2012 በጀት ዓመት ኢተምድ በሶስቱም የስራ ዘርፎች 30‚033 የአገልግሎት ጥያቄዎች ተቀብሎ በማስተናገድ ሸማቹ ለሚከፍለው ዋጋ ጥራቱ ተመጣጣኝ የሆነ ምርትና አገልግሎት እንዲያገኝ በማስቻል ለፍትሃዊ የንግድ ውድድር አስተዋፅኦ ለማበርከት እና የህብረተሰቡን ጤናና አካባቢያዊ ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ አካላትም ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት በመስጠት ትርፋማና ውጤታማ እንዲሆኑ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡ የእቅዱ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርበዋል፡ በፍተሻ ላቦራቶር ለ18,567 በኢንስፔክሽን ለ9,524 እና በሰርቲፊኬሽን ለ1‚184 የአገልግሎት ጥያቄዎች በመቀበልና በማስተናገድ እሴት የሚጨምር የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር ይሰራል፡፡