የፓምፖችን የጥራት ፍተሻ የሚያከናውን ማእከል ለማቋቋም የሚያስችል በጀት Small Scale & Micro Irrigation Support Project (SMIS) ከተባለ የውጪ ግብረ ሰናይ ድርጅት በመገኘቱ  pump performance test and engine test የተባሉ የ2 መሳሪያዎች ግዥ በመፈፀም ላብራቶሪው ተተክሎ ስራ ለመጀመር ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የፍተሻ ስራዎችን ቀጣይ የአካሄድ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ስራውን ለማስጀመር ግብርና ሚ/ር፣ ኢተምድ እና ኤስ.ኤም.አይ.ኤስ(SMIS) በመነጋገር የጥራት ፍተሻ ስራውን ለማስጀመር ማእከሉ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡