የደን ሀብትን ማብዛት እየተከሰተያለውን የአፈር መሸርሸር፣የበረሃማነት መስፋፋትና የብዝሐ ሕይወት መመናመን በመግታት የግብርናውን ዘርፍ ልማት በማፋጠንና በማስቀጠል ምርታማነቱን ለመጨመርና  የምግብ  ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ድርሻ ያለው በመሆኑ፤መንግስት ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃያ ወጣቸውን ፖሊሲዎችና እና ስትራቴጂዎች ለማስፈጸም  በየዓመቱ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አመራር እና ሰራተኞችም ይህንን አገራዊ አላማ በመደገፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀንን በማስመልከት “50ኛው ዓመት 50ሺ ችግኝ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የጥራት ቁጥጥር ስራ የተጀመረበትን 50ኛ ዓመት ለመዘከር በኦሮሚያ ክልል በሰበታ  ደበል ተራራ አካባቢ በሁለት  ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አከናውነዋል፡፡